በድሬዳዋ አስተዳደር በለገዲኒ ገጠር ቀበሌ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ በመከናወን ላይ ይገኛል

የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሀ መዓድን እና ኢነርጂ ቢሮ በለገዲኒ ገጠር ቀበሌ በቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት አማካኝነት ቁፋሮው እየተከናወነ የሚገኘው የመጠጥ ውሀ ኘሮጀክት ምልከታ አካሄዷል።

በለገዲኒ ገጠር ቀበሌ ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ ችግር ይስተዋል የነበር ሲሆን ይህን የሚቀርፍ የ330 ሜትር ርቀት ላይ የወጣውን የጥልቅ የጉድጓድ ውሃ የአካባቢውን የመጠጥ ውሀ ችግር ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በሙከራ የውሃ አቅሙ ከ20 ሊትር በሰከንድ በላይ የሚሰጥ መሆኑም ታውቋል፡፡

አቶ ፉዓድ መሀመድ መይደኔ የውሃ ማእድንና ኢነርጂ ፅ/ቤት ኃላፊ በወቅቱ እደተናገሩት የህዝብን ጥያቄ መመለስ የቻለ ስኬት ሲሆን እንደ መንግስት ከፍተኛ ትጋት በማድረግ የዛሬውን ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል፡፡

በቀለአድ ወረዳ ለገዲኒ ቀበሌ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ ስኬታማ በመሆኑ ውሃ የወጣ ሲሆን በዛሬው እለት ይህንኑ ስራ የውሃ ማእድንና ኢነርጂ ፅ/ቤት ኃላፊ እና የቆላማ አካባዎች የኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ኢሳም ሁሴን በጋራ ጉብኝት አከናውነዋል፡፡

ላለፉት በርካታ ወራት ሲደረግ የነበረው የቁፋሮ ስራ ተጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት በቀጣይ ጠንካራ ርብርብ ይደረጋል ሲሉ ስራ አስኪያጁ ጠቅሰዋል፡፡በቀጣይ በቅርብ ግዜያት ውስጥ በዚህ በወጣው ከፍተኛ ውሃ ላይ በመመርኮዝ ጥናት በማከናወን የቡዙ መንደሮች የመጠጥ ውሃ (Multi Village Water Supply) እና ለመስኖ አገልግሎትም እንዲሆን በማስቻል የልማት ስራዎች እንደሚሰሩ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *