በፈረንሳይ ሌጉ ከተማ ከንቲባ የተመራ ልዑካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎበኘ

ልዑኩ በጉብኝቱ የድሬዳዋን ነፃ የንግድ ቀጠናን፣ ደረቅ ወደብን፣ አዲሱ ምድር ባቡርን እንዲሁም የድሬዳዋ ኮንቬንሽን ማዕከልን እና የድሬዳዋ አለም አቀፍ እስታድየምን ተመልክቷል።

የፈረንሳይዋ ሌጉ ከተማ ከንቲባ ሊዮኒዳስ ሰርጅ በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን እድገት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያፋጥን ገልፀው፤ የጉብኝቱ ዋንኛ ዓላማም የልምድ ልውውጥ ለማረግ እንዲሁም በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ለመመልከት መሆኑን አብራርተዋል።

ከንቲባው አያይዘውም በቀጣይ የድሬዳዋን ታሪክ እና የአኗኗር ዘይቤ በጠበቀ መልኩ የቱሪዝም ዘርፉን የማሳደግ ስራ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *