ልኡክ ቡድኑ ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ጋር በጋራ በመሆን በክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ፓርክ አረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ በድሬዳዋ የነበረውን የልምድ ልውውጥ አጠናቋል።
በዚህም የፈረንሳይ ለቡግ (Le Bugue) ከተማ ከንቲባ ሊዮኒዳስ ሰርጅ ችግኝ መትከል አካባቢያችንን ለመጠበቅ እንዲሁም ነፋሻማ አየር ለማግኘት ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ገልፀዋል።
ከንቲባው አያይዘውም ድሬዳዋ ለአረንጓዴ አሻራ ከፍተኛ ትኩረት ሰታ እየሰራች የምትገኝ ከተማ መሆኗን መመልከታቸውን ገልፀው ይህም በቀጣይ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው አመላክተዋል።
የልኡክ ቡድኑ አባላት በበኩላቸው በድሬዳዋ አረንጓዴ አሻራቸውን በማሳረፋቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ በድሬዳዋ ቆይታቸው በርካታ ተሞክሮዎችን ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።


