የካፍ ልዑክ ቡድኑ በመጀመሪያ የድሬዳዋ ስታድየም አጠቃላይ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በተጨማሪም የድሬዳዋ ሆቴሎች እና ሆስፒታሎችን ተዟዙረው ተመልክቷል ።
የድሬዳዋ ስታዲየም ገምጋሚ ልዑካን ቡድኑ በካፍ ኢንስፔክሽን ቢያንካ ብሬንዳ ሲመራ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ላይሰንሲንግ ዳይሬክተር አቶ አመሀ ተስፋዬ ፤ የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሐመድ ናቸው።
የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን የድሬዳዋ ስታዲየምን የካፍን መስፈርት ለማሟላት በርካታ ማሻሻያዎች አድርጓል ።


