በድሬዳዋ አስተዳደር በማህበረሰቡ እና በአመራሩ ቅንጅታዊ አሰራር መዳበር ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸው ተገለፀ
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል። ልዑኩ ከድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ከክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ከክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ ጋር በጋራ በመሆን የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠናን፣ ደረቅ ወደብን፣ በኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ…


