የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የእውቅና ሽልማት በትላንትናው እለት አበረከተች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በ44 ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የእውቅና ሽልማት አበረከተች።

ሽልማቱን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ለከንቲባው ተወካይ እና የድሬዳዋ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ ለአቶ ገበየሁ ጥላሁን አስረክበዋል።

ከንቲባ ከድር ጁሀር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በምሥራቅ ኢትዮጵያ ለምታከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት ያለ አድሎ በፍትሐዊነት መንግሥታዊ ኃላፊነታቸውን በመወጣት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ነው ሽልማቱ የተበረከተላቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *