ልዑክ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ በክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ልዑክ ቡድኑ በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኝም ከወዲሁ ተጠቁሟል።
በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት በክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራ ልዑካን ቡድን ሀገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ ላይ ለመሳተፍ ድሬዳዋ ከተማ ገባ


