በድሬዳዋ ደወሌ የምድር ባቡር ድርጅት ባቡር ላይ በደረሰ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፋን የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ገለጸ

ከትላንት በስቲያ መነሻውን ከደወሌ አድርጎ በመጓዝ ላይ በነበረው የህዝብ ማመላለሻ ባቡር ባጋጠመው ድንገተኛ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፉን የድሬዳዋ ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አየለ ወልደዮሀንስ በዛሬው እለት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

በአደጋውም ሳቢያ 1የድርጅቱ ሰራተኛ እና 14መንገደኞች ህልፈት የደረሰ ሲሆን 28 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት፣ 13 ሰዎች ቀላል የህክምና እርዳታ አግኝተዉ ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሲሆን 2 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶል በአጠቃላይ በአሁኑ ሰዓት 7 ሰዎች በሆስፒታል በህክምና እርዳታ ላይ እንደሚገኙ ኃላፊው ገልጸዋል።

ባቡሩ 8 ጋሪ፣ 6የጭነት ጋሪ እና 2 የመንገደኞች ጋሪ ይዞ ከደወሌ ተነስቶ ወደ ድሬዳዋ ሲያደርግ በነበረው ጉዞ ላይ በሶማሌ ብሔራዊ ክልል ሽንሌ ከተማ ሲደርስ ጋሪው ተመልሶ በምድር ባብቡር ድርጅት ውስጥ ቆሞ ከነበረ የሰራተኛ ባቡር ጋር በመጋጨቱ ምክኒያት አደጋው መፈጠሩን ኃላፊው ገልጸዋል።

አደጋው የደረሰው ቦታ አቀበታማ በመሆኑ ባቡሩ የጭነት ጋሪውን ለሁለት ከፍሎ 4የጭነት ጋሪ ወደ ድሬዳዋ ካደረሰ በኃላ ቀሪውን ለማድረስ ተመልሶ10 ደቂቃ ከተጓዘ በኃላ በተፈጠረ አደጋ መሆኑን አስረድተዋል።

በተፈጠረው አደጋ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይኖር በማድረግ በኩልም በአስተዳደሩ የተደረገው ርብርብ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በደረሰው ጉዳትም አስተዳደሩ እና ድርጅቱ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

አስተዳደሩ በዘላቂነት ጉዳት የደረሰባቸውን ቤተሰቦች ለመደገፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል ።

አደጋው በደረሰበትም ወቅትም የሺኒሌ ሲቲ ዞን፣ ወረዳ እንዲሁም የአስተዳደሩ ነዋሪ ላደረጉት ከፍተኛ ርብርብም ምስጋና አቅርበዋል።

የድሬዳዋ-ደወሌ የባቡር ድርጅት በሳምንት ሁለት ጊዜ መንገደኞችን እና የኢንዱስትሪ ግብአቶችን እያጓጓዘ የሚገኝ ሲሆን ድርጅቱ በባለፉት 3 ወራትም 3,975 መንገደኞችን እና ከ4ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ,እቃ ማጓጓዙንም ኃላፊው አስረድተዋል ።

የድሬዳዋ-ደወሌ ምድር ባቡር ድርጅት ስራ ከጀመረ ምንም አይነት አደጋ ያላጋጠመው መሆኑ ያነሱት ኃላፊው ድርጅቱ በቀጣይ ጥቂት ጊዜያት ውስጥ አገልግሎት እንደሚጀምር ኃላፊው ጨምረው ገልጸዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *