ተረጂነት የመፍጠር አቅም እና የመሥራት ጉልበትን የሚበላ ካንሰር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ለምክር ቤቱ ምላሽ እና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ መሥራት እየቻለ ተረጂ የሆነ ሰው በዕድሜ የገፋ ቢሆንም በዚህ ምክንያት ተገቢውን አክብሮት እንደማያገኝ ነው አክለው የተናገሩት።
ኢትዮጵያውያን ለክብራችን ስንል ከተረጂነት መላቀቅ አለብን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ፖለቲካ ሳይሆን የኢትዮጵያ ክብር ጉዳይ ነው ብለዋል።
መረዳት መጥፎ ሱስ መሆኑን በመግለጽም፣ ራስን የመቻል እሳቤ በሁሉም ዘንድ ሊሰርፅ እንደሚገባ ነው የተናገሩት።


