በድሬዳዋ የወረዳ ሁለት ወጣቶችና ስፖርት ማስተባበሪያ ከኢለፈንት ቢት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጁትና ለ 8 ቀናት ሲካሄድ የቆየው የ “ሳቢያን ካፕ” ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
በዚህም በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳ 02 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አቤል ምስራቅ የሳቢያን ሲቲ ካፕ የእግር ኳስ ውድድር 8 ቡድኖችን ባሳተፈ መልኩ ሲካሄድ መቆየቱን ገልፀው፤ ውድድሩ ወንድማማችነትን በማጠናከር ስፖርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ተካሂዶ መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ውድድሩ በአንደኛ ደረጃ ዲቪዚዮን የሚወዳደሩ ተጫዋቾች ከዲቪዚዮኑ በፊት ቀድመው እንዲዘጋጁና የአሸናፊነት ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ቡድኖችን በማበረታታት ወደ ዋናው ዲቪዚዮን ለማስገባት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም አቶ አቤል ጨምረው ገልፀዋል።
አቶ አቤል አያይዘውም እንደነዚህ አይነት ውድድሮች ወጣቶች ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያጠፉ ከማድረጉ በተጨማሪ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የጎላ ሚና እንዳላቸው አመላክተዋል።
በመጨረሻም አቶ አቤል ለድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን እንዲሁም ለድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽንና በአጠቃላይም ለውድድሩ መሳካት የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በውድድሩ ታይዋን ቡድን ሀድወናግን 1-0 በማሸነፍ የዋንጫና የገንዘብ ተሸላሚ ሆኗል።


