ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናችዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ጥሩ ውይይት አድርገናል። ውይይታችን በኢኮኖሚ እና ዘላቂ የመሠረተ ልማት ጉዳዮች ላይ አተኩረን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን የምናጠናክርባቸውን እድሎች አስመልክቶ የተካሄደ ነበር። ብራዚል በቅርቡ የተካሄደው የCOP30 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ COP32ን በኢትዮጵያ ስናዘጋጅ ከብራዚል የምንወስደው ብዙ ጠቃሚ ልምዶች አሉ። የአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራን የሚያራምድ በሚገባ የተሰናዳ መስተንግዶ እንዲኖረን ከልምዶች የተገኙ ሃሳቦችን መለዋወጡን አጠናክረን ለመቀጠል አቅደናል።

ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አህመድ (ዶ/ር )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *