በ10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የድሬዳዋ አስተዳደር አፈጻጸም ሪፖርት ተገመገመ

10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም በሰመራ ሎጊያ ከተማ ከህዳር 6 እስከ 10 መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ወደ ስፍራው ያቀናው የአስተዳደሩ ልዑክ ቡድን የተሳትፎ የአፈጻጸም ሪፖርት በአስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ ተገምግሟል።

በመድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማት ስራ አስኪያጅ ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም አስተዳደሩ በዘንድሮ የከተሞች ፎረም ከዚህ ቀደም ከነበረው ተሳትፎ የተሻለ ስራዎች ይዞ መቅረቡን ጠቅሰው በ14 ዘርፍ እና በ2 ኢንሼቲቨ የተሰሩ የልማት ስራዎችን በማቅረብ አስተዳደሩን ማስተዋወቅ የተቻለ ሲሆን በዚህም አበረታች ውጤት ማምጣት መቻሉን ተናግረዋል።

አስተባባሪ ኮሚቴ እና ልዑክ ቡድኑ የነበረውን ቅንጅታዊ ስራ የሚደነቅ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው በፎረሙ የተሳተፉ አካላትንም በሙሉ አመስግነዋል።

በሪፖርቱም የተገኙ ልምድና ተሞክሮ በማካፈል ረገድ ከተማችን ድሬ የአንድ ማዕከል ወደ ስራ መግባቱ ከመሬት አስተዳደር ካዳስተር ስራዎች ከቤቶች ልማት ጋር በተያያዘ አስተዳደሩ ለሌሎች ከተሞች ልምድ ማካፈል እና መውሰድ መቻሉ በሪፖርቱ ተብራርቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *