የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ የ2018 ዓ.ም የበጋ ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎትን አስመልክቶ የፅዳት ዘመቻና የችግኝ እንክብካቤ አከናውነዋል።
በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ ከወጣቶች ጋር በመተባበር የፅዳት ዘመቻ መከናወኑን እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ መሰራቱን ገልፀዋል።
በተለይም ወጣቶች ሁሌም በበጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ በመሰማራት አካባቢያቸውን የመንከባከብና ማህበረሰባቸውን የመጥቀም ስራ መስራት እንደሚገባቸውም አቶ ኢብራሂም አመላክተዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ ቤት ጊቢን ምቹና ሳቢ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ኃላፊው ጠቁመው፤ በጊቢው የሚገኙ መሬቶችን በማልማት እና “ምግቤን ከጓሮዬ” በሚል ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በመትከል
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አያይዘው ገልፀዋል ።
በቀጣይም ሰፋፊ መሬት ያላቸው ሁሉም ተቋማት ይሄንን ተሞክሮ በማስፋትና የተለያዩ ተክሎችን ከጓሮአቸው በመትከል የስራ ቦታቸውን ማልማት ይገባቸዋል ሲሉ አቶ ኢብራሂም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመርሃ-ግብሩ ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው ወጣቶች በበኩላቸው ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በየጊዜው መንከባከብ ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል።
በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ወጣቶቹ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ አከናውነዋል።


