በዚህም ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት፣ ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንዲሁም ለድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የፓርቲ አባላት ስልጠናው መሰጠት ጀምሯል።
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት በመደመር መንግስት እይታ የግብርና የገጠር የመዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ፣ የከተማ ልማት እንዲሁም የቱሪዝም ዘርፍ እመርታ በሚሉት ርዕሶች ላይ የሚሰጥ ይሆናል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የሀገራዊ ማንሠራራትን ግብ ለማሳካት፣ ተቋማዊ ቅንጅትን ለማጠናከር እና በብልፅግና ፓርቲ አባላት መካከል የአመለካከት እና የተግባር አንድነትን መፍጠር መሆኑ ተመላክቷል።
በአጠቃላይም በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በመፍጠን እና በመፍጠር ለመስራት ስልጠናው አጋዥ መሆኑ ተጠቁሟል።


