“በመደመር መንግስት እይታ፣የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ለድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የሚሰጠው ስልጠና መካሄድ ጀምሯል

ለ3ኛ ዙር “በመደመር መንግስት እይታ፣የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ስልጠና ለንግድ፣ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ፣ጤና ቢሮ፣ግብርና ውሃ እና ማዕድን ቢሮ፣ብዙሃን እና መገናኛ ድርጅት፣ የሰነዶች ምዝገባ ና ማረጋገጫ አገልግሎት፣የከተማ ልማት ናኮንስትራክሽን ቢሮ እንዲሁም ለመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።

እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በዋናነት የብልጽግና ፓርቲ ለዘርፎች ያለው እይታ ፤ዘርፎች ለሃገረ መንግስት ግንባታ ያላቸውን አስተዋጽዖ አመራሩ እና አባላቱ በአግባቡ እንዲረዳ የሚያስችል ስልጠና መሆኑ ተገልጿል።

የመንግስት ሰራተኛ አባላቶች በብልጽግና መነፅር እና እሳቤ ሆኖ ተግባራትን በማከናወን የሚመራውን ህዝብ እንዲለወጥ ከማድረግ አኳያ ሁሉም የብልጽግና አባላት የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት እንደሆነም ነዉ የተገለጸው።

ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በቱሪዝም፣በግብርናና ገጠር ልማት፣በኢንዱስትሪ እና በከተማ ልማት ዘርፍ እንደሚሰጥ ታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *