“በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት ለድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የፓርቲ አባላት እና ሰራተኞች የተዘጋጀው ሶስተኛ ዙር ስልጠና መካሄድ ጀመረ።

“በመደመር መንግስት እይታ፤ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት ለድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የፓርቲ አባላት እና ሰራተኞች የተዘጋጀው ሶስተኛ ዙር ስልጠና መካሄድ ጀምሯል።

በስልጠናው መክቻ ላይ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሹክሪ አብዱረህማን እንደተናገሩት ስልጠናው በዋነኝነት በግብርናው፣ በማኑፋክቸሪንግ ፣ በቱሪዝም እንዲሁም በከተማ ልማት ዘርፎች “በመደመር መንግስት ዕይታ ፤ የዘርፎች ዕመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኛኞች እና የፓርቲ አባላት በዘርፎቹ ላይ በብልፅግና ዕሳቤ ተገቢው ግንዛቤ ኖሯቸው ለውጡን በእውቀት መደገፍ የሚያስችላቸው አቅም የሚፈጥሩበት ስልጠና ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

ተቋምን ስንመራም ሆነ አገልግሎትን ስንሰጥ ሀገራዊ ተልእኮዎችን ተረድተን ቀጣይ ሀገራዊ አቅጣጫዎች ላይ በቂ ግንዛቤን በመጨበጥ ለሀገራዊ ብልፅግናችን እንድንተጋ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል።

በባለሙያው የአመለካከትና የተግባር አንድነትን በመፍጠር ባለሙያው የብልፅግና እሳቤን በተጨባጭ እንዲተገብር ስለሚያስችል ሰልጣኝ በቆይታቸው ሁሉ ስልጠናውን በከፍተኛ ዲሲፕሊን እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

በመድረኩም የግብርና እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ላይ በቀረበ ሰነድ መድረኩ ተጀምሯል።

መረጃው የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *