በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ ሶስተኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም የመንግስት ሰራተኞች የአባላት ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ በሚል መሪ ቃል በግብርናና ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ለድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት እና ለድሬደዋ አስተዳር ለዋናው ኦዲት ቢሮ የመንግስት ሰራተኞች አባል የተዘጋጀ ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል ።

በስልጠና መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ከሪማ አሊ ፓርቲያቸው ብልፅግና የሀገራችንን ስብራቶችን ለመጠገን በተለይ በማህበራዊ በፖለቲካዊ በኢኮኖሚያዊ ያሉ ስብራቶችን ለመጠገንና ሁለተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል ።

በስልጠና መዉሰድ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ በተግባር ዉጤት በማምጣት በማንሰራራት ላይ ያለችዉን ሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልፅግና ማረጋገጥና እዉን ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት ነዉ ብለዋል ።

በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክርቤት የፖለቲካ ዘርፍ አማካሪ አቶ ማርቆስ ባዩ በመደመር መንግስት እይታ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ለመላዉ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበዉ ዉይይት ተደርጎበታል ።

እንዲሁ በተመሳሳይ በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ በሚል መሪ ቃል በግብርናና ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ለሴቶች፣ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ለወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች አባላት የተዘጋጀ ስልጠና ተሰጥቷል ።

በተዘጋጀው የስልጠና መድረክም የሴቶችና ህፃናት የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሰራተኛና ማህራዊ ጉዳይ ኤጀንሲጨዠ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱረህማን ሙሳ የግብርና እና ኢንዱስትሪ ዘርፍ እምርታ ለብልጽግና ፓርቲ አባላት ስልጠና የተዘጋጀውን ሰነድ አቅርበዉ ዉይይት ተደርጎበታል ።

“በመደመር መንግስት እይታ፥ የዘርፎች እምርታ” ሶስተኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ የመንግስት ሰራተኞች የአባላት እየተሰጠና የሚገኘዉ ስልጠና በነገዉ እለትም የሚቀጥል ይሆናል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *