የድሬዳዋ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ እንዲሁም የፐብሊክ ሰርቪስ እና የፍትህ ፀጥታ ቢሮ ህብረት የብልፅግና ፓርቲ ሀብረት አባላት የሦስተኛ ዙር ስልጠና መስጠት ተጀመረ።

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ስልጠና ላይ የቢሮው አባላት “በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ” እንዲሁም “እምቅ አቅማችን ለመዳረሻ ግባችን” በሚል መሪ ቃል ሥር በብዝሃ ዘርፍ ስኬት ላይ ትኩረት አድርገው እየሰለጠኑ ይገኛሉ።

የሥልጠናው ዋና ዓላማ የሀገራዊ ማንሠራራትን ግብ ለማሳካት ተቋማዊ ቅንጅትን ለማጠናከር እንዲሁም በብልፅግና ፓርቲ አባላት መካከል የተቀራረበ አመለካከትን መፍጠር መሆኑ ተነስቷል።

በስልጠናው ወቅት ተሳታፊዎቹ የመደመር መንግስት ባህሪያትና እይታዎች ምንድን ናቸው? በሚለው ፅንሰ ሃሳብ ላይ ሰፊ ግንዛቤን እያገኙ ይገኛሉ። በተጨማሪም የዘርፎችን ትስስር በማጎልበት ተቋማት የተጠናከረ ቅንጅት በሚታይበት መንገድ ሥራዎችን ማከናወን እንዳለበት ተገልጿል።

የሥልጠናው ዋና መነሻ “የብዝሃ ዘርፍ ስኬት ለሀገራዊ ማንሠራራት!” የሚለው መርህ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ የብልፅግና ፓርቲ በልማት ዕቅዱ ውስጥ ያስቀመጣቸውን እምቅ አቅም ለመዳረሻ ግብ ለማድረስ፣ “አንድ አመት እንደ አምስት አመት በብርቱ ትጋት!” የሚል የትጋት ጥሪ ቀርቧል። ይህም የሁለት ቀናት ስልጠና አባላቱ በሀገር ግንባታ ሂደት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዲወስዱ ለማነሳሳት ያለመ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *