”በመደመር መንግስት እይታ ለዘርፎች አመርታ” በሚል መሪ ቃል ለድሬዳዋ አስተዳደር የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና ለገቢዎች ባለስልጣን የብልጽግና ፓርቲ ህብረት 3ኛ ዙር ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።
ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን “የግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን” ፣”ኢንዱስትሪን ዘርፍ እምርታ” የቱሪዝም እና የከተማ ልማት እምርታ ላይ የሚያተኩሩ ሰነዶች የሚዳሰሱ ሲሆን በቀረቡት ሰነዶች ላይ ጥልቅ ውይይት እንደሚደረግ ታውቋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር የገቢዎች ባለስልጣን ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱሰላም መሐመድ በወቅቱ እንደተናገሩት፣ ስልጠናው በሁሉም የአመራር እርከኖች ላይ ሆነ ወጥ የሆነ ግንዛቤ ለመፍጠር እና ብቁ፣ርዕይ ያለውና ታታሪ አመራርና ሰራተኛ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል ።
በተጨማሪም፣ በፓርቲው የተቀመጡትን ሀገራዊና አስተዳደራዊ የልማት አቅጣጫዎች አባላቱ በተገቢው መንገድ ለማስፈጸም የሚያስችል ብቃትና ወጥ የሆነ የእውቀት ደረጃን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ጨምረው ተናግረዋል።


