የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ “ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ “በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን ) ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አክብሯል።
በአስተዳደሩ”ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ 16ቱ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን ንቅናቄ በተለያዩ ሴቶችን ከጾታዊ ጥቃት ለመታደግ በሚረድ ተግባራት ሲከናወን መቆየቱን እና በዛሬው እለትም ሰው ተኮር በሆኑ ተግባራት አረጋውያንን የመደገፍ ስራ መከናወኑን የድሬዳዋ ሴቶች ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሌሊሴ አህመድ ገልፀዋል።
በንቅናቄ ቀናቱም የሴቶች ጥቃት አስከፊነት ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀው ድርጊቱን በመከላከል ረገድ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በዛሬው በ16ቱ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን ንቅናቄ የማጠቃላያ መርሃ ግብርም ሰው ተኮር በሆኑ ተግባራት በአረጋውያን መጦሪያ ማዕከላት በመቆዴያን ፣በአሰገደች እና በዳዊት አረጋውያን መርጃ ማዕከላት የተለያዩ የአልባሳት ድጋፍ ተካሂዷል።


