14 ሚሊየን የሚገመት የስራ ቦታ ደህንነት መጠበቂያና የውሃ መሳቢያ ፓንፕ በልማታዊ ሴፍቲኔት መረሃ ግብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በመረሀ -ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በአስተዳደሩ ለገጠር ልማት ትኩረት በመስጠት በገጠር ምርታማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የልመናና የተረጂነት አስተሳሰብ በመቀየር በቤተሰብ ደረጃ በምግብ እራስን ለመቻል የሚያስችሉ ስዎችን ጨምሮ እንደ አገር የተቀመጡ የልማት ኢኒሺቲቮች ግብ እንዲመቱ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
አንድም የሚለማ መሬትረ ፆሙን እናዳያድርና ያለውን የውሃ ሃብት በአግባቡ ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነት ማሳደግ አርሶ አደሩ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለገበያ ጭምር ማምረት እንዲችልና የገጠር ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ እንደ መንግስት እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
የብልፅና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ መንግስት እንደ አገር የጀመረውን ተረጂነትን ዜሮ የማድረግና በራስ አቅም ለዜጎች የሰበአዊ ድጋፍ የማቅረብ አላማ እንዲሳካ በየደረጃው ያለ አመራር የተጣለበትን ሀላፊነት የመወጣት ግዴታ እንዳለበት አሳስበዋ፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር የውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑረዲን አብደላ ባለፉት አመታት እንደ አስተዳደር በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር በተለይም የመስኖ ልማት ስራን በማስፋፋት ፤ አነስተኛ መስኖ ልማት ቴክኖሎጂንና የውሃ እቀባ ዘዴዎችን በስፋት በመጠቀም ሰፊ አቅም ለመፍጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡በገጠሩ ማህበረሰብ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመቅረፍ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በፕሮግራሙ ተጠቃሚ ለሆኑ የኑሮ ማሻሻና ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች ላይ ተሰማርተው ጥሪት እንዲያፈሩና ኑሮአቸው እንዲሻሻል የሚያስችል የተሟላ ስልጠና በመስጠት በዘንድሮ አመት ለ7510 እማ/ አባዎች በነፍስ ወከፍ 33.300 በድምሩ ከሁለት መቶ ሃምሳ ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ስርጭት ለተጠቃሚዎች መደረጊን አቶ ኑረዲን ጠቁምዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃ ማእድንና ኢነርጂ የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ፈንዲሽ ባሻ በሌላ በኩል የውሃ ማሰባሰብ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ የተሻሻለ የመስኖ ውሃ አማራጭ ያላቸውን ቀበሌዎች በጥናት በመለየት በአጠቃላይ 200 ተጠቃሚዎች በመመልመልና በቡደን በማደራጀት ስምንት ሚሊየን ብር ሰባ ስድስት የውሀ መሳቢያ ፓንፖች በተጨማሪም የምርጥ ዘር አቅርቦትና የሙያ ድጋፍ እንደተደረገላቸው አስረድተዋል ፡፡ከዚህ በተጨማሪም በስድስት በሚሊየን ብር ለማህበረሰብ ስራ ቀያሾችና ተቆጣጣሪዎች የተገዙ የስራ ቦታ ደህንነት መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በዚህ አመት በጀት መባቻ አጠቃላይ የምርታማ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች 26971 ተጠቃሚዎች በሚደረግላቸው ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ክትትል ከፕሮግራሙ እንደሚሰናበቱ ለማወቅ ተችሏል፡፡


