የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወረዳ 8 የዕቅድ አፈጻጸምን ገመገመ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወረዳ 8 የዕቅድ አፈጻጸማቸውን የገመገመ ሲሆን በልማት፣ በመልካም አስተዳደር ከነዋሪው ጋር የተቀናጀ የሰላም አደረጃጀት በመፍጠር በተለይ በፀጥታ ዘርፍ ላይ ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን የወረዳ 8 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ አሜ ለቋሚ ኮሚቴ አብራርተዋል፡፡

በተከበሩ አቶ አህመድ አብደላ ሰብሳቢነት የሚመራው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የወረዳ 8 የዕቅድ አፈጻጸማቸውን የተመለከተ ሲሆን ከኮሚኒቲ ፖሊስና ከፀጥታ አካላት ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ያሉ የወጣት አደረጃጀቶች፣ የሰላም አደረጃጀቶች ሊበረታቱ የሚገቡ መሆኑን አንስተው ባለመዘናጋት በዚሁ ሊቀጥሉ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ወረዳ 8 የሚሰጠውን አገልግሎት ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና የሚታዩ ውስንነቶች ደግሞ እንዲታረሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የኮሪደር ልማት ስራ ወረዳው ላይ ለወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠረ የተነገረ ሲሆን አካባቢውን ማስዋብ ጥቅሙ ለህብረተሰቡ መሆኑን ታውቆ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ተብሏል፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የህግ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አህመድ አብደላ በወረዳው የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆኑን አንስተው ከህንፃ ግንባታ ጋር ተያይዞ ለተነሳው ጥያቄ በሂደት የሚፈታ መሆኑ በውይይቱ ላይ የተገለፀ ሲሆን ወረዳው አሁን ላይ ባለው የስራ አፈፃፀም ቀልጣፋ መሆን እንዳለበትና ከመታወቂያ አሰጣጥ ጋር ተያይዞ እንዲሁም ሌሎች ምላሽ የሚሹ የህብረተሰቡ ጥያቄዎች መፍትሄ እንዲበጅላቸው አቅጣጫ ሰጥተዋል።

ቋሚ ኮሚቴው በወረዳ 8 ውስጥ ባደረገው ግምገማ፤ የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክረው እንዲቀጥሉና በወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ አሜ በተነሳው የህንፃ ግንባታ ጥያቄ ቋሚ ኮሚቴው ጥያቄውን ወደ ሚመለከተው አካል በመውሰድና አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ለወረዳው እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *