“በወረዳዎች እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች በአስተዳደር ደረጃ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ እያፋጠኑ ይገኛሉ”- የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም::

በወረዳዎች እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች በአስተዳደር ደረጃ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ስራ እያፋጠኑ ይገኛሉ ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢንጂነር ጀማል ኢብራሂም ተናገሩ።

በድሬዳዋ አስተዳደር በዘጠኙም የከተማ ወረዳዎች በማህበረሰቡ ድጋፍ እየተተገበሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎች ለከተማዋ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ መሆኑን ኢንጂነር ጀማል ገልፀዋል።

የምዕራፍ ሁለት የኮሪደር ልማት ስራ በምዕራፍ አንድ ስራ የተገኙ ልምዶችን በመቀመር እየተተገበረ እንደሚገኝ ኢንጂነር ጀማል ጠቅሰው በቀጣይም ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ሁሉም የድሬዳዋ ማህበረሰብ የኮሪደር ልማቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመደገፍ ልማቱ እንዲፋጠን እያበረከቱት ላለው አስተዋፆ ኃላፊው ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም ተቋሙ የደረቅና ፍሳሽን ማስወገጃ፣የተጠራቀመ ደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀም በሚያስችል እና ፍሳሽ ቆሻሻውን ደግሞ አጣርቶ መጠቀም የሚያስችል ፕሮጀክት 1.2 (ከአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር )በላይ ወጪ በማድረግ እያከናወነ እንደሚገኝ ኢነጂነር ጀማል ጠቁመው፤ በአስተዳደሩ ኤክስፖርትን ታሳቢ ተደርጎ የተገነባው ዘመናዊ የቄራ አገልግሎት ስራ መጀመሩ ጥራትን በማሳደግ ረገድ አይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም አብራርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *