የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3 ተኛ የስራ ዘመን 5 ተኛ ዓመት 11 ኛ መደበኛ ጉባኤውን በአሁን ሰዓት እያካሄደ ይገኛል::

በጉባኤውም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የምክር ቤቱ 3 ተኛ የስራ ዘመን 5 ተኛ ዓመት 11 ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የምክር ቤቱን 3 ተኛ የስራ ዘመን 5 ተኛ ዓመት 3 ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የአስተዳደሩ የአስፈፃሚና ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የ 2018 ዓ.ም የ 6 ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ይቀርባል።

ከዚህ በተጨማሪም በጉባኤው የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ግዢ እና የንብረት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ተወያይቶ ማፅደቅ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የአስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም ተግባርና ሀላፊነታቸውን ለመወሰን የወጣውን ረቂቅ ማሻሻያ አዋጅ ተወያይቶ ማፅደቅ ።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ፅህፈት ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተውያይቶ ማፅደቅ ፣ ከሀላፊነት የተነሱ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት መሪዎች ፣ ከፍተኛ ሀላፊዎች ፣ የምክር ቤት አባላት የፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች እና ዳኞች የሚያገኟቸውን መብቶችና ጥቅሞች ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 28\2012 ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ ናቸው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *