“ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ፍትህንና ማህበራዊ መስተጋብርን በማረጋገጥ ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ ነው”:-የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አብዲ ሙክታር
ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ፍትህንና ማህበራዊ መስተጋብርን በማረጋገጥ ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባኤ ክቡር አቶ አብዲ ሙክታር ተናገሩ። በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በአገር በቀል የዳኝነት እና የሽምግልና ስነ-ስርዓትን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ስልጠና ሰጥቷል። በዚህም በስልጠናው መርሃ-ግብር የተገኙት የተከበሩ አቶ አብዲ ሙክታር ባህላዊ የሽምግልና ስርዓት እና ፍርድ ቤቶች በማህበረሰቡ ዘንድ…


