“የትምህርት ጥራት፣ተደራሽነትና ብቃትን የሚያጎለብቱ የትምህርት ግቦችን ለማሳካት እየተሰራ ነዉ..” የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ100 ቀናት እቅድ ውስጥ የትምህርት ጥራት፣ብቃትን የሚያጎለብቱ የትምህርት ግቦችን ለማሳካት እየሰራ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አልይ አስታወቁ ።

በ100 ቀናት እቅድ ውስጥም የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የመማር ማስተማር ሂደቱን የተማሪ፣ የመምህራን የወላጅ የግንኙነቶችን በማጠናነር የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል።

የትምህርት ጥራት፣ብቃትን የሚያጎለብቱ የትምህርት መስክ ግቦችን ለማሳካት ደረጃውን የጠበቀ የተማሪዎች በተለይም የስድስተኛ እና የስምንተኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በተክኖሎጂ በመታገዝ የዲጂታል አገልግሎት ስራዎችን መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በቴክኖሎጂ በትምህርት መስክ የመምህራን እና የተማሪዎች የ5ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እና የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እንዲወስዱ በማስቻል የእቅዱን 80 በመቶ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።

በተለይም ደግሞ ከትምህርት ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት፣የተማሪ ውጤትን ማሻሻል፣ መጽሃፍትን ተደራሽ ማድረግ፣ የመምህራን ስልጠና የማጠናከሪያ ትምህርት ፣ተከታታይ ምዘናና የንባብ ክህሎትን ማዳበር የሚሉ ግቦች ላይ በመቶ ቀናት እቅድ ውስጥ ተካተው እየተሰራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።

የትምህርት ቤቶች የምገባ ፕሮግራምን በአስተዳደር ደረጃ የትምህርት ቤቶች የምገባ ኤጀንሲ በካቢኔ ደንብ ማቋቋም መቻሉንም ገልጸዋል ።

በመሆኑም በተያዘው የትምህርት ዘመን በአስተዳደሩ የተማሪዎችን የብሄራዊ ፈተናዎች ውጤት ለማሻሻል ለ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ምርጥ ተሞክሮ ለሁሉም

የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ትምህርት አመራርና መምህራን ለማስፋት የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *