ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤት ባደረጉት ማብራሪያ፤ የትግራይ ሕዝብ አሁን ካለበት ችግር ወጥቶ ራሱ ተግቶ ሠርቶ መለወጥ የሚፈልግ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው ብለዋል።
የትግራይ ሕዝብ ሰላም፣ ልማት ይፈልጋል፤ ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያውያን ጋርም በጋራ መሥራትና ማደግ ይፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
ነገር ግን የትግራይ ሕዝብ በፖለቲካ አውድ ውስጥ መድረክ እንጂ ተዋንያን መሆን አልቻለም፤ መድረኩን ሌሎች ይጫወቱበታል እንጂ ራሱ አይጫወትም ብለዋል።
በትግራይ ያሉ ፖለቲከኞችም ከአጃቢ ተዋንያን ወደ መሪ ተዋንያን መሸጋገር እንዳለባቸው አመላክተው፤ የትግራይ ሕዝብ በፖለቲካ አውድ ውስጥ ተዋንያን መሆን አለበት ብለዋል።
በመሆኑም የትግራይ ሕዝብ በራሱ ተዋንያን መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለዚህ ደግሞ አዲስ የፖለቲካ አስተሳሰብ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።
“EBC


