በአስተዳደሩ ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ በጤናው ዘርፍ እምርታ ተመዝግቧል.. የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ

የአስተዳደሩ ነዋሪዎችን በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ፍትሃዊ ጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እና ሞዴል የጤና ስርዓትን ለመገንባት በጤናው ዘርፍ እምርታ ተመዝግቧል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ አስታወቁ፡፡

ቢሮው በመቶ ቀናት እቅድ ውስጥ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራ መከናወኑን ገልጸው በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግ አሰራሮችን ወደ ዲጂታል የመቀየር ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱን ገልጸዋል።

በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እንዲሁም የወረርሽኝ እና ድንገተኛ አደጋዎች ጥቆማ አስተያየቶች እና ቅሬታዎችን ለመቀበል ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የነፃ የስልክ መስመር አገልግሎት ተግባራዊ መሆኑን ተናግረዋል።

የስራ ቦታን ምቹ ከማድረግም አንጻር በ100 ቀናት እቅድ ውስጥ የተቋሙን ተገልጋይ የሚበዛበት የአገልግሎት ዘርፍ በመለየት ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ስራ መሰራቱንም ገልዋል።

በተጨማሪም የጤናው ዘርፍ የአንድ ማዕከል የመረጃ ቋት (data mangement center) የመረጃ ማእከል በዘላቂነት የጤናውን ዘርፍ ለመገንባት የሚያስችል የመረጃ ማዕከል መቋቁሙንም ነዉ ኃላፊዋ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ የገለጹት።

ፈጣን የሆኑ የመረጃ ልውውጦችን ለማድረግ የሚያስችል one office የሚል ሶፍት ዌር በማበልጸግ 18ቱንም በአስተዳደሩ የሚገኙ ሆስፒታል፣ ጤና ጣቢያ እና ጤና ኬላዎችን በቀጥታ የሚያገናኝ እና በዛው ልክ የክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ስራዎች ለመጀመር ዝግጅት ማለቁንም አስረድተዋል።

የጤና መድህን አገልግሎቶችንም ከፋይዳ መታወቂያ ጋር በማስተሳሰር 2,947 የጤናው ሴክተር ሰራተኞች ሙሉ ለሙሉ የፋይዳ መታወቂያ በማውጣት ወደ አገልግሎት የማስገባት ስራ መስራቱን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *