ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን እንዲሁም በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በርብርብ እንደሚሰራ ተገለፀ::

‎”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ ሀሳብ በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተዘጋጀ የግማሽ ዓመት ማጠቃለያ ኮንፈረንስ በድሬዳዋ አስተዳደር ተካሂዷል።

በዚህም ‎በመድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የዕቅድ አፈፃፀም በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ በአቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ በፍጥነት በመጨመር በቀጣይ ዓመታት ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በርብርብ መስራት እንደሚገባ አመላክተዋል።

ተሳታፊዎቹ አያይዘውም በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚጠበቅብንን ሚና ለመወጣት ዝግጁ ነን በማለትም ተናግረዋል።

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒ በማድረግ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲቻል በትኩረት እንደሚሰራም የመድረኩ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

በአጠቃላይም ተሳታፊዎቹ ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን እንዲሁም በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በርብርብ እንደሚሰራ ገልፀው በቀረበው ሪፖርት ላይ ሀሳብ አስተያየት ሰተዋል።

ከመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ በአቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ምላሽና መብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከንቲባ ከድር ጁሀር ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችንም አስቀምጠዋል።

በመርሃ ግብሩ የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሪፖርት በድሬዳዋ አሰተዳደር የኢንስፔክሽን እና የስነ ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ ሰብሳቢ ፋኪያ መሃመድ ቀርቦ የተመዘገቡ ውጤቶችና በሥራ ሂደት ያጋጠሙ ተግዳሮቶችም ተዳሰዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ የብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በሙሉ ድምፅ ፀድቆ መድረኩ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *