“ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” ! በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተዘጋጀ የግማሽ አመት ማጠቃለያ ኮንፍረንስ መካሄድ ጀምሯል።
በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አብዲ ሙክታር፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ም/አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከሴክተር ቋማትና ከወረዳዎች የተውጣጡ የብልፅግና አመራርና አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በኮንፍረንሱ ዙሪያ ያሉ አጠቃላይ መረጃዎችን እየተከታተለ የሚያደርሳችሁ ይሆናል::


