“ለዘላቂ ሰላም ግንባታ እና የአየር ንብረት ለዉጥ መፍትሔዎች ወጣት መር ጥረቶችን ማበረታታት ” በሚል መሪ ሀሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር አዘጋጅነት የአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም በትናንትናው እለት መጀመሩ ይታወሳል ። ፎረሙ በዛሬው እለትም የቀጠለ ሲሆን በአየር ንብረት ለውጥ እና ሊደርሺፕ ላይም ውይይት አድርገዋል ።
የአየር ንብረት ለውጥ በሀገራችን ፣ በአህጉራችን ብሎም በአለማችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከሚያደርሱት ውስጥ አንዱ እና ዋንኛው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም ላይም በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ የሚነሱትን ሀሳቦች በቀጣይም በተግባር ሊሰራባቸው እንደሚገባም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የአየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት አቶ ታጁዲን አብዱላሂ ያስታወቁት ።
የአፍሪካ ቀንድ የወጣቶች ፎረም በድሬዳዋ መካሄዱ በተለይም ስለ ሀገራችን እድገት እና ብልፅግና ብሎም በቀጣይ ሀገራችን ኢትዮጲያ ለመስራት ያቀደቻቸውን ፕሮጀክቶች ለጎረቤት ሀገራት የምናሳውቅበት ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥርም ነው የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወጣት ሀሚድ አብደላ ያስታወቁት ።
በፎረሙ ላይም ከጂቡቲ ፣ ከሶማሊያ ፣ ከሶማሌላንድ ፣ ከደቡብ ሱዳን ፣ የኢጋድ እና የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች ፣ የኢትዮጲያ ወጣቶች ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚ እና ፕሬዝዳንት እንዲሁም የየክልሉ የወጣት ምክር ቤት ስራ አስፈፃሚዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።


