“ለዜጎች ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት እየተሰጠ ነዉ… ” የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ

በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ለህብረተሰቡ ቀልጣፋ እና ውጤታማ አገልግሎት መሰጠት መቻሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይር ሀጅኑር አስታወቁ።

በአስተዳደሩ የመንግስት ተቋማትን በመጀመሪያ ምዕረራፍ ወደ ሪፎርም በማስገባት እና የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ዘርፈ ብዙ ስራዎች መከናወኑን ገልጸዋል።

ተቋሙ በመቶ ቀናት እቅድም የተቋማትን አገልግሎት ለማሻሻል የሰራተኛውን አቅም በማጎልበት እንዲሁም የተገልጋይን እንግልት የሚቀንስ ሁሉን በአንድ ቦታ አገልግሎት የሚያገኙበትን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በአስተዳደሩ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።

በመሆኑም በማንዋል ሲሰጡ የነበሩ72 አገልግሎትን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሙሉ ለሙሉ በዲጂታል በመቀየር በኦንላየን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል።

በዚህም 12,730 አገልግሎቶች የተሰጡ ሲሆን በቀጣይም 32 አገልግሎቶችን ወደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልጸዋል።

በመቶ ቀናት እቅድም ወደ መሶብ የአንድ የማዕከል አገልግሎት የገቡ እና ለሚገብ 250 አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞችን የአቅም ግንባታ የተሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል።

በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር በክቡር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ኢንሼቲቭ የተጀመረው የ5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በአስተዳደሩ ለ3,380 ሰራተኞችን የዲጂታል ክህሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ታቅዶ 1,686 ሰራተኞች ስልጠናውን ሙሉ ለሙሉ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *