መጋቢት 10/2018 ዓ.ም
ለመሆኑ ተገቢ ያልሆኑ የነዳጅ አጠቃቀሞች የትኞቹ ናቸዉ?
1ኛ:- መኪናው ሳይንቀሳቀስ ሞተሩን ብቻ አስነስቶ መቆየት።
መኪናው ሳይንቀሳቀስ ሞተር አስነስቶ ለረጅም ደቂቃዎች መቆም በዜሮ ኪሎ ሜትር እየተጓዙ ነዳጅ ማቃጠል ነው።
2ኛ:- ከመጠን በላይ የሆነ ፍጥነት:: መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ሲነዳ የንፋስ ግፊት ስለሚጨምር ሞተሩ ያንን ተቋቁሞ ለመጓዝ ብዙ ነዳጅ ይጠቀማል።
3ኛ:- በድንገት ፍጥነት መጨመርና በድንገት ፍሬን መያዝ ነዳጅን በከፍተኛ ሁኔታ ያባክናል።
4ኛ:- በመኪናው ውስጥ ወይም በመኪናዉ ላይ የማያስፈልጉ ከባድ ዕቃዎችን መጫን ሞተሩ ጉልበት እንዲያወጣ ስለሚያደርገው የነዳጅ ፍጆታን ይጨምራል።
5ኛ:- የትራፊክ መጨናነቅ፦ “ሄድ ቆም“ የበዛበት እንቅስቃሴ ሞተርን ስለሚያደክም ነዳጅ ይበላል፡፡
6ኛ:- በዝቅተኛ ማርሽ ለረጅም ጊዜ ማሽከርከር ነዳጅ ያባክናል፡፡
7ኛ:- ተሽከርካሪን በመደበኛነት አለማስመርመር እና የነዳጅ ቆጣቢ የአነዳድ ዘይቤን አለመለማመድ ነዳጅ እንዲባክን ያደርጋል
8ኛ:- ለጽዳት ስራ መጠቀም፤- እንደ ልብስ፣ ወለል ወይም የመኪና ሞተር ያሉ ነገሮችን በቤንዚን ወይም በናፍጣ ማጽዳት
9ኛ:- ለማገዶ፣ ለከሰል ወይም ለቆሻሻ ማቃጠያነት ነዳጅን መጠቀም
10ኛ:- ለጀነሬተር እና ለምግብ ማብሰያ የሚዉሉ የነዳጅ አጠቃቀሞችን ማስተካከል አለበቻል
11ኛ:- ነዳጅን በፕላስቲክ፣ በባልዲ ወይም ተገቢ ባልሆኑ እቃዎች ውስጥ ማስቀመጥ ነዳጅ እንዲባክን ያደርጋል
12ኛ:- ነዳጅን ደህንነቱ ባልተጠበቀ ቦታ ማስቀመጥ፤ ነዳጅን ደህንቱ ባልተጠበቀ ቦታ ማስቀመጥ ነዳጅ እንዲባክን ከማድረጉም በላይ ለአደጋ ያጋልጣል
ተገቢ ባልሆኑ የነዳጅ አጠቃቀሞች ዙሪያ ተጨማሪ ሃሳብ ካሎት ያጋሩን !


