መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ስልቶች ይፋ ማድረጉን ገለጸ

በመካከለኛው ምስራቅ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ መንግሥት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ስልቶች ይፋ ማድረጉን የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ጽ/ቤት ገለጸ።

የአስተዳደሩ የንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚኑ ጣሀ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትና ዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ ያጋጠመውን ችግር ለመቋቋም የሚያስችሉ ውሳኔዎችን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) የሰጡትን መግለጫ ተከትሎ እንደ አስተዳደሩ ያሉ ወቅታዊ የነዳጅ አቅርቦትን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመካካለኛው ምስራቅ ያለው ጦርነትና አለመረጋጋት በሀገራችን የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ እንዲሁም መንግሥት የሚከተላቸውን አቅጣጫዎች በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

መንግስት ከዚህ ቀደም በነዳጅ ዋጋ ላይ በየጊዜው ከነፍጣ ከ1ሊትር ላይ 95 ብር እንዲሁም ቢንዚል ላይ በሊትር 42 ብር ድጎማ የሚያደርግ ስሆን በአጠቃላይ እስከ 20 ቢሊዮን ብር ድጎማ ያደርጋል ብለዋል።

መንግሥት የተፈጠረውን የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍና ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች እንዳይገቱ ነዳጅን ከተጓዳኝ ገበያ ስለሚገዛና የዓለም የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት በሦስት እጥፍ ዋጋ እየገዛ ለማቅረብ መገደዱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የተፈጠረውን የነዳጁ አቅርቦት እጥረትን ተገን በማድረግ የታሪፍ ዋጋ ጭማሪ አዝማሚያዎች እንዳሉ እና ይህን በሚያደርጉ አካላት ላይጥብቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ነው ኃላፊው ያስታወቁት።

በመሆኑም ያጋጠመውን የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በሀገርና በዜጎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጫና እንዳያሳድርና በፍትሐዊነት ለመምራት የሚያስችል ውሳኔ ማሳለፉን ገልጸዋል።

በዚህም መሠረት

1. ነዳጅ የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች በማደያ የቅድሚያ ቅድሚያ እንዲሰጣቸው፣

2. ከፍተኛ አምራችና የኤክስፖርት ድርጅቶች በቀጥታ፣

3. ልዩ ትኩረት የሚሹ የመንግሥትና የግል ፕሮጀክቶች በቀጥታ፣

4. የገቢና ወጪ ንግድን ጨምሮ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን የሚያጓጉዙ ተሽከርካሪዎች

5. ግብርናን የሚያዘምኑ ሞተሮች፣

6. የከተማና ሀገር አቀፍ የብዙሃን ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች

7. እንዲሁም በናፍጣ የሚሰሩ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ነዳጅን በቅድሚያ እንዲያገኙ የሚያደርግ የቅድሚያ የነዳጅ አጠቃቀም አሠራር የሚተገበር መሆኑን ገልጸዋል።

8 የጸጥታ ተቋማት፣የጤና ተቋማት እና ሌሎች ልዩ ልዩ ዘርፎች እንደየአስፈላጊነቱ የሚጠቀሙ ይሆናል።

ከሕብረተሰቡ የሚከጠበቁ ተግባራትም

1) ነዳጅን በቁጠባ እንዲጠቀም፣

2) የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ስልትን መከተል፣

3) የእግር ጉዞ ባህልን ማጎልበት

4) አላስፈላጊ የጉዞ ፕሮግራሞችን መሰረዝና ማቆም

5) የሕዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም የሚሉ አማራጫችን አስቀምጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *