በሰነ ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ የብልፅግና ፖርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳሰ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያሰ ጅራ፣ የድሬደዋ ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኻሊድ መሀመድ እንዲሁም የሊግ ካምፖኒ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።
በዕለቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አሰተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንደተናገሩት በውጤቱ ተደስተናል እንኳን ደሰ አላችሁ፤ ድሬደዋ ከ5 አመታት በኋላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በሜዳው እንዲጫወት ማስቻሏ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም እንዲሁ በድሬደዋ ዓለም አቀፍ ስታዲየም መጫወታቸው ለድሬዳዋ ትልቅ ስኬት ነው፤ ለወደፊትም ትልልቅ ጨዋታዎችን ለማዘጋጀት ዝግጁ ነን ብለዋል ።
አቶ ሀርቢ አክለውም ድሬዳዋን የስፖርት ማዕከል እንድትሆን እየሰራን ነው፣ ለስኬቱም የተለያዩ አካላቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ በአስተዳደሩ ስም ጥሪዬን አቀርባለው ብለዋል ።
የድሬደዋ ወጣቶች ና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኻሊድ መሀመድ በበኩላቸው እንደተናገሩት ይህ ጨዋታ በድሬዳዋ እንዲካሄድ ብዙ አካላቶች አሰተዋጽኦ አድርገዋል፤ ለዚህም እናመሰግናለን፤ በቀጣይም በድሬደዋ ስታዲዮም የሚቀሩ ትንንሽ ስራዎችን ለማሟላት እንሰራለን ብለዋል ።
የኢትዮጵያ እግር ኳሰ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያሰ ጅራ በበኩላቸው እንደተናገሩት ከውጤቱ በላይ በሜዳችን ከ5 አመታት በኋላ መጫወታችን ነው ያሰደሰተን፤ ሜዳውን ለጨዋታ ዝግጁ ላደረጋችሁት አካላቶች ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፤ እናመሰግናለን ብለዋል።
በመጨረሻም የሊግ ካምፖኒ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የኢትዮጵያ ፕርሜርሊግ በቀጣይ አመት ወደ ድሬደዋ ሊመጣ እንደሚችል ተናግረዋል።


