የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 1 ለ 0 በማሸነፍ በድምር ውጤት ደግሞ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት ወደ ምድብ ማጣርያ መግባቱን አረጋግጧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድኑ የዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን በሀገሩ ምድር እንዲያደርግና በደጋፊው ታጅቦ ለድል እንዲበቃ የተደረገው ብሔራዊ ርብርብ እጅግ የሚደነቅ ነው ። በዚህ ታሪካዊ ሂደት ውስጥ የድሬዳዋ ከተማን ለዚህ ጨዋታ ዝግጁ በማድረግና የኢትዮጵያን ስም በከተማዋ ላይ ከፍ በማድረግ ረገድ ባለፍት አመታት የአስተዳደራችን ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ከፍተኛ አስተዋፆ አድርገዋል ።

በተለይም የስታዲየሙን ደረጃ ለማሻሻልና ለካፍ ( CAF ) መስፈርት ብቁ እንዲሆን ክቡር ከንቲባችን ያደረጉት አስተዋፆ ትልቅ ነው ፣ ስፖርት ለከተማዋ እድገትና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለውን ፋይዳ በመረዳት ላበረከቱት አስተዋፆ ሁሉ ትልቅ ክብር እና ምስጋናም ይገባቸዋል ።

በዛሬው እለት በነበረው የእግር ኳስ ጨዋታ ላይም ከባድ ዝናብ ጥሎ የነበረ ሲሆን ነገር ግን የዘነበው ዝናብ ጨዋታውን ሳያስተጓጉል ኢንተርናሽናል ስታዲየማችን የካፍ ( CAF ) መስፈርትን አሟልቶ መሰራቱን በተጨባጭ ያስመሰከረበትም ጨዋታ ሆኗል።

ከዚህ በዘለለም የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ እና የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ እና የስራ ሀላፊዎች በተለይም የእግር ኳስን ቴክኒካዊና አስተዳደራዊ ሂደት በብቃት በመምራት ረገድ ያሳዩት ትጋት ለዚህ ውጤት አብቅቷል ። የአስተዳደሩ ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካሊድ መሀመድ እና የኮሚሽኑ የስራ ሀላፊዎች እና ባለሞያዎች ካፍ ለዚህ ጨዋታ ስታዲየሙ ሊያሟላቸው የሚገባቸውን ስራዎች ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተሟልተው ደጋፊው ስታዲየም ውስጥ ገብቶ ጨዋታ እንዲከታተል ትልቅ አስተዋፆ ተወጥተዋል ።

በዛሬው እለት ዋሊያዎቹ በድሬዳዋ ምድር እንዲህ አምሮባቸው በሙሉ የሀገር ፍቅር ባይተዋርነት ሳይሰማቸው በደጋፊዎቻቸው ፊት ለውጤት እንዲበቁም የአስተዳደራችን ነዋሪዎች ሚና የላቀ ነበር ።

ከልብም እናመሰግናለን !

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *