የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን አሸነፈ

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የዋልያዎቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ቸርነት ጉግሳ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡

በድምር ውጤት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ድልድል ላይ መካተት ችላለች፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *