***********************
መጋቢት ለኢትዮጵያውያን የድል መባቻና የለውጥ ወጋገን የቀደደበት ወር ነው። ባለፉት ስምንት የለውጥ ዓመታት ሀገራችን ሕልውናዋን የሚፈታተኑ “የሦስትዮሽ መከራዎችን” (Triple Shocks) ማለትም ደም አፋሳሽ ጦርነትን፣ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጫናን እና የተፈጥሮ ፈተናዎችን በጽናት ተሻግራለች።
ኢትዮጵያ ትፈርሳለች ብለው ያሟረቱ ሁሉ የሕዝቧን አይበገሬነት ዘንግተውት ነበር። ዛሬ ግን ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር አዳዲስ ታሪኮችን እየጻፍን እንገኛለን፦
ከስንዴ ተረጂነት ወደ ላኪነት፦ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የታሪክ ጠባሳችንን በመደምሰስ ስንዴን ወደ ውጭ መላክ ጀምረናል።
የሉዓላዊነት ምልክት፦ የዓባይ ግድብ (ሕዳሴ) በዲፕሎማሲያዊና በገንዘብ እገዳ ሳይበገር ግንባታው ተጠናቅቆ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል።
የከተሞች ገጽታ ለውጥ፦ በአዲስ አበባና በ75 ከተሞች የተጀመረው የኮሪደር ልማት ከተሞቻችንን ለነዋሪዎች ምቹና ውብ አድርጓቸዋል።
ዓለም አቀፍ ተሰሚነት፦ የብሪክስ (BRICS) አባልነት፣ የባሕር በር ጥያቄን ወደ ዲፕሎማሲያዊ አጀንዳነት ማሸጋገርና የዲጂታል ኢትዮጵያ (5 Million Coders) ስኬቶች የነገዋን ብልጽግና ዛሬ ላይ መሠረት ጥለዋል።


