<<ድሬዳዋን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች ሳቢ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ ነው።>>

አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ

#DGC | መጋቢት 23 /2018

በድሬዳዋ አስተዳደር በሆቴልና ቱሪዝም እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ በግንባታ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።

ድሬዳዋን የቱሪስት እና የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በሆቴል ኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶች ተጀምረው በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ ሲሆን በዘርፉ እየተከናወነ ያለው የኢንቨስትመንት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሚገኝ በምክትል ከንቲባው ተጠቁሟል።

ድሬዳዋን በተለያዩ የቱሪዝም ዘርፎች ተመራጭ ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ያሉ ሲሆን በዘርፉ የሚያስፈልጉ አገልግሎቶች እንዲስፋፉና እንዲዘምኑ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ሀርቢ አክለው ገልፀዋል።

በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ እነዚህ ሆቴሎች ሲጠናቀቁ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር እና የአስተዳደሩን ኢኮኖሚያዊ ገቢ በማነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ ተናግረዋል።

የአስተዳደሩ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት በዘርፉ የሚያደርገውን ክትትልና ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እንዲሁም ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲኖር የሚያስችሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አቶ ወንደሰን ጨምረው ገልፀዋል።

በመስክ ምልከታው የተቃኙት ሆቴሎች ከባለ አራት እስከ ባለ ስምንት ወለል ህንፃዎች ሲሆኑ ፣ ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎችን ጨምሮ ደረጃቸውን የጠበቁ የመሰብሰቢያ አዳራሾችንና የተለያዩ አገልግሎቶችን የያዙ ናቸው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *