በመካከለኛው ምስራቅ ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በነዳጅ አቅርቦት ላይ በሀገራችን ብሎም በአስተዳደራችን እጥረት ተስተውሏል፤ ከዚህም የነዳጅ እጥረት ጋር ተያይዞ የአስተዳደሩን ነዋሪዎች ያነጋገርናቸው ሲሆን አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ በአስተዳደሩ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ተናግረዋል።
ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ የነዳጅ እጥረት ቢከሰትም ነገር ግን በአንዳንድ ነዳጅ ማደያዎች አሁንም ድረስ ነዳጅ እየተሸጠ መሆኑን ተናግረው በቂ ነዳጅ እያላቸው ነዳጁን ለገበያ በማያቀርቡ ነዳጅ ማደያዎች ላይም የክትትል እና ቁጥጥር ስራ መሰራት እንዳለበትም አስታውቀዋል ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም ነዳጅን በብላክ ማርኬት የሚሸጡ አካላት ላይም ህጋዊ እርምጃ መወሰድ እንዳለበትም ነው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ያስታወቁት ።


