በድሬዳዋ አስተዳደር በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጪዎችን ይፋ አድርጓል
የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመርሃ ግብሩ እንደተናገሩት በባለፉት ዓመታት ድሬዳዋ የሰላም ተምሳሌት ሆና እንድትቀጥል በአብሮነት በፍቅር ተባብሮ በመስራት ከፍ ብላ እንድትታይ ላደረጉት ተሳትፎ ለህዝቡ ምስጋና አቅርበዋል።
በዛሬው እለትም ብልጽግና ፓርቲ ለሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለአስተዳደሩ ምክር ቤት 37 እና 1የፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረባቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎችን ሲያቀርብ በትምህርት ዝግጅታቸው ፣ በሥራ ልምዳቸውና በታታሪነታቸው የተመሰከረላቸው ናቸው ብለዋል።
ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች ቢመረጡ ህዝባችንን እና ፓርቲያችንን በቅንነትና በታማኝነት እንደሚያገለግሉ የታመነባቸው መሆኑንም ነው ክቡር ከንቲባ ያስረዱት።
በ7ኛው ዙር የምርጫ ጊዜ አስተዳደሩን የሚወክሉ እጪዎች ሀሳቦቻችንን የሚያዳምጡ ጉዳዮቻችንን በጥልቀት የሚረዱ እንዲሁም ባላቸው የካበተ የሥራ ልምድ ለከተማው ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰሩም ገልጸዋል።


