ኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስት ምስረታ በምርጫ ብቻ ሊሆን እንደሚገባ አንዳንድ የድሬዳዋ ኗዋሪዎች ተናገሩ። በሰላማዊ መንገድ የመንቀሳቀስ ዓላማ የሌላቸውና በውጭ ሀገራት የሙገኙ አፍራሽ ኃይሎች ከውጪ ሀገር እየነዙ ያሉትን የውሸት ወሬዎች እንደማይቀበሉም አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ካነጋገራቸው ነዎሪዎች መካከል ኑሯቸውን በከባድ መኪና አሽከርካሪነት የሚመሩት አቶ ወርቅነህ ድሬዳዋ ላይ ከምሽቱ ስምንት ሰዓት እንኳ ብትመጣ በሰላም መንቀሳቀስ ተችላለህ ። በእጅህ ኖረህ ያየኸውን ሰላም ከውጪ ሆነው እንዲበጠብጡ አልፈቀውድም ፤ ሌሎችም እንዳይፈቅዱ አበረታታለሁ ብለዋል ፡፡

ሌላው የድሬዳዋ ኗሪ በበኩላቸው በውጪ ሀገር ሆነው እኛን ወክለው ሊናገሩ አይችሉም ፤ ስለእኛ ለመናገር ሀገር ውስጥ ገብተው ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ ሊያቀርቡ ይገባል ያሉ ሲሆን ማህበረሰቡ የሚያዳምጠውን ሚዲያ መምረጥ እንደሚገባውም አሳስበዋል ፡፡

እነሱ እኛን አይወክሉም ያሉ የድሬዳዋ ኗዋሪ እነሱን ሰምቶ ለአመጽ የሚንቀሳቀስ ከሰለ የሚያመው መሆን አለበት ፡፡ ሰላመችንን በመስጠበቅ ሰላማዊ ምርጫ እነደርጋለን ብለዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *