ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የድሬዳዋ-ሺኒሌ አስፓልት መንገድ በይፋ ተመረቀ
በድሬዳዋ አስተዳደር እና በሶማሊ ክልል መካከል ያለውን የንግድና የማህበራዊ ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል ተብሎ የሚጠበቀው የድሬዳዋ-ሺኒሌ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ፕሮጀክት ተጠናቆ በይፋ ተመረቀ። ለዚህ ግዙፍ የመሠረተ ልማት ግንባታ ከ1.3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉ ታውቋል። የመንገድ ፕሮጀክቱን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደን ፋራህ እንዲሁም የሶማሊ…


