የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በዛሬው ዕለት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል። 1ኛ:- ካቢኔው በቀዳሚነት የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ፕላን ሥራዎች ላይ በመወያየት ውሳኔ አስተላልፏል። የከተማ ፕላን ሥራዎች የድሬዳዋን ፈጣን ዕድገት በስልታዊ መንገድ ለመምራት ከፍተኛ ሚና አላቸው። የመኖሪያና የንግድ ቀጠናዎችን በዘመናዊ አሠራር በመለየት ለቀጣይ መሠረተ ልማት፣ ለኢንቨስትመንት መስፋፋት እና ለከተማዋ ውበት ምቹና ዘላቂ መሠረት…


