ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ አፈጻጸም ግምገማውን አጠናቀቀ::
ብልፅግና ፓርቲ በጅግጅጋ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በስኬት አጠናቋል። የብልፅግና ፓርቲ የብሔራዊ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ የሚከተሉት አበይት ጉዳዮች ተገምግመዋል:: ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዕቅዱ መሠረት በቅድመ ምርጫ እና በምርጫው…


