ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ አፈጻጸም ግምገማውን አጠናቀቀ::

ብልፅግና ፓርቲ በጅግጅጋ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደትና የፓርቲውን የምርጫ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በስኬት አጠናቋል።

​የብልፅግና ፓርቲ የብሔራዊ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በተገኙበት በዚህ መድረክ ላይ የሚከተሉት አበይት ጉዳዮች ተገምግመዋል::

​ፓርቲው በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዕቅዱ መሠረት በቅድመ ምርጫ እና በምርጫው ወቅት የነበሩትን ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞች በዝርዝር ለይቷል።

​ በድህረ ምርጫ ወቅት ትኩረት በሚሹ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት በመደረግ የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

​የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ለተሳታፊ አመራሮቹ፣ ለክልል ርዕሳነ መስተዳድሮችና ለከንቲባዎቹ የሶማሌን ሕዝብ ወግና ባህል የሚያንጸባርቁ የባህላዊ አልባሳትና የተለያዩ ማስታወሻ ስጦታዎችን አበርክተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *