በአትሌቲክስ ምስራቁን የሀገራችን ክፍል ወጣቶች ዉጤታማ ለማድረግ በጋራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

    ምስራቁን የሀገራችን ክፍል ማለትም የሶማሌ ክልል፣ የሀረሪ ክልል፣ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌን እና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የአትሌቲክስ ፍላጎትና ተሰጦ ያላቸዉን ወጣቶች ዉጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል መሰረታዊ ድጋፍ በማድረግ በአትሌቲክስ ምስራቁን የሀገራችን ክፍል ወጣቶች ዉጤታማ ለማድረግ በጋራ እየተሰራ መሆኑ የድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የኮሚሽነሩ ተወካይ እና ወጣቶችን የማሳተፍና ማብቃት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር አቶ እስክንድር አህመድ ገለፁ ፡፡
    ቡድኑ ልምምድ ሲያደረጉ እያበረታታ አግኝተን ያነጋገነዉ የኮሚሽነሩ ተወካይ አቶ እስክንድር እንደ ገለፁልን ወጣቶች በማህበር ተደራጅተዉ ለድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን የአትሌቲክስ ቡድን ለሟቋቋም ጥያቄ ማቅረባቸዉንና በጥያቄያቸዉ ዙሪያ ዉይይቶች ሲደረጉ እንደነበሩና መሟላት ያለባቸዉን ቅድመ ሁኔታ ካሟሉ በኃላ ዕዉቅና አግኝተዉ የአፍረንቀሎ አትሌቲክስ ቡድን መመስረቱንና ይህ የተመሰረተዉ የአፍረንቀሎ አትሌቲክስ ቡድን በምስራቁ የሀገራችን ክፍል መጀመሪያ የተመሰረተ የአትሌቲክስ ቡድን እንደሆነና ይህን ቡድን የመጀመሪያ እንደመሆኑና ለሀገራችን ስፖርት በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ያሉ ተሰጦና ፍላጎት ያላቸዉ ወጣቶች በተለይም በአጫጭር ሪቀቶች ዉጤታማ ማድረግ እንዲችሉ በጋራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
    በአፍረንቀሎ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ልምምድ ሲያደረጉ አግኝተን ካነጋገርናቸዉ መካከል አሰልጣኝ ጀማል ቡቁ ወደ አፍረንቀሎ አትሌቲክስ ቡድን የሚቀላቀሉ ተሰጦና ፍላጎት ያላቸዉ ወጣቶችን በተዘጋጀ ዉድድር የተሻለ ዉጤት ያስመዘገቡትን በዉጤታቸዉ መሰረት የቡድኑ አባል መደረጉን አብራርተዋል፡፡
    የቡድኑ አባላት የሆኑት ሙሉጌታ ፈጠነ እና ሻሜ አብዱረህማን በበኩላቸዉ የዚህ ቡድን መመስረት በአትሌቲክስ ዉጤታማ የመሆን ፍላጎታችንን እንድናሳካ በሚደረግልን ድጋፍ የሚረዳቸዉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡