20 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በድሬዳዋ ለመገንባት በሚቻልበት ዙሪያ ዉይይት ተደረገ

    በድሬዳዋ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በስፋት እየታየ ያለዉን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት 20 ሺ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በድሬዳዋ ለመገንባት በሚቻልበት ዙሪያ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የፌደራል መንግስት በተለይም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ዉይይት ተደረገ ።
    በዚህ ውይይት ላይ በድሬ ደዋ እድገት ላይ እንቅፋት የሆኑ ከቻርተሩ የተገናኙ የህግና የአሰራር ማነቆዎች ተፈትሽዉ ሊፈቱ ይገባል ተብሏል፡፡
    አስተዳደሩ በቀጣይ 20,000 መኖሪያ ቤቶች ለመገንባት ለያዘው እቅድ የቦንድ ብድር ፋይናንስ አቅርቦት እንዲያገኝና አሁን በአስተዳደሩ በጀት እየተገነቡ የሚገኙ ቤቶች ከባንክ ጋር እንዲተሳሰሩ በማድረግም የፌደራል መንግስት አወንታዊ ሚና ሊጫወት ይገባል ተብሏል ።
    የአስተዳደሩ አፈጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ፣ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ እንዲሁም በም/ከንቲባ ማዓረግ የንግድ ኢነደስቲሪና ኢነቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ተወካዮች እንዲሁም የአስተዳደሩ የመንግሥትና የድርጅት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በውይይቱ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል ።