በአስተዳደሩ ብሎም ኦሮሚያ ክልል በምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ እንዲሁም በሶማሌ ክልል የተከሰተውን የበረሃ የአንበጣ ለመከላከል የተወሰዱ ያሉትን ሥራዎች አበረታች ውጤት ማስመዘገብ እንደተቻለ ተገለጸ፡፡

    በምስራቁ የአገራችን ክፍል አጎረባች ክልሎች ከባለፈው ዓመት አጋማሽ ጀምሮ የተከሰተውን የበረሃ አንበጣ ለመከላክል የተደረጉ የማጥፋት ዘመቻ እና የደረሰውን ውድመት የአስተዳደሩ ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢኔርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እና የኦሮሚያ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ የአንበጣ መከላከል ግብረ ሃይል የሥራ እንቅስቃሴና የተገኙ ውጤቶችን ለሚዲያ ባለሞያ መግለጫ ሰተዋል፡፡
    ግብረ ሃይሉ ባሳለፍናቸው ሳምንታት የአንበጣ መንጋው በደረሱ ሰብሎችና በክብት ግጦሽ የሚውሉ ቁጥቋጦ ላይ ጉዳት ማደረሱ ተናግሮ በተለይም በአንድ አንድ በአስተዳደሩ ሥር ላሉት ገጠር ቀበሌዎችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ጉዳት ማድረሱና ወደ ኦሮሚያ ምስራቅና ምዕራብ ሀረርጌ ዞኖችና ሀረሪ ክልል በመዝመቱ አስቀድሞ በተሰራው የቅንጅት ሥራዎች የከፋ ጉዳት ሳያደርስ ግብረ ሃይሉ እንደተቆጣጠረ የኦሮሚያ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ ተናግረዋል፡፡
    የበረሃ አንበጣ መንጋው ከየመንና ከሶማሊላንድ ሀገሮች በምስራቁ የሀገራችን አጎረባች ክልሎች በሶማሌ ክልል፣ ድሬዳዋ፣ሀረር እና በምስራቅና ምዕራብ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች መከሰቱን ተከትሎ የአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት እና በተለይ ጥሩ ልምድ ባገኙበት የሌሊት የኬሚካል ርጭት የበረሃ አንበጣው መጥፋቱን የድሬዳዋ ግብርና ወሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ገልጸዋል፡፡ አቶ ኢብራሂም አክሎም የበረሃ አንበጣው ያደረሰውን ጉዳት ምን ያህል እንደሆነ በሄክታር፣ በሰብል ዓይነትና በአጠቃላይ ምን ያህል አርሶና አርብቶ አደር አባወራ እንዲሁም በኢኮኖሚ ላይ ያደረሰው ጉዳት በቅርብ ጊዜ ተጠናቆ ይፋ እንደሚያደረጉት ተናግረዋል፡፡
    ግብረ ሃይሉ በቀጣይ በተለይም በሶማሌ ክልል በረሃማ ቦታዎች አንበጣው እንቁላል በመጣሉ ይህን የአንበጣ መንጋ በድጋሚ እንዳይከሰት የማጥፋት ሥራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ታውቀዋል፡፡