በስነ ስርአቱ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ፤ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር፤የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ፤የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ ፤ የኢፌደሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ አየር ሀይል እና እዝ የበላይ አመራሮች እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባ ገዳና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል፡፡
በስነ-ስርአቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስ እንደተናገሩት በድሬደዋ አስተዳደር በገጠሩም ሆነ በከተማ የሚኖሩት ነዋሪዎች ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን በመሆን የሚቻለውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ሙሉ ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል፡፡
የከተማችን ባለሀብቶች ለሰራዊቱ የሚያስፈልገውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በአስተዳደር ደረጃ የመንግስት ሰራተኞች ፤ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም መላው የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ደማችን ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን በሚል መሪ ቃል በነገው እለት ህዳር 5/3/2013 ዓ.ም የደም ልገሳ ፕሮግራም እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡
የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ በስነ-ስርአቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክትም የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሀገራችንን የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ትግል በመደገፍ የዋሄል ክላስተር እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማመስገን የድሬደዋ አስተዳደሩ የመከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ በሚያስፈልገው ሁሉ ከጎኑ መሆኑን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ በጸጥታ ስራ ለተሰማሩ የፀጥታ ሃይሎች ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አበርክተዋል፡፡የአስተዳደሩ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በርክክብ ስነ ስረአቱ ላይ ተገኝተው ድጋፉን የተረከቡት የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ አየር ሀይል ምድብ ዋና አዛዥ ኮሮኔል አበበ ለገሰና የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሮኔል ብርሀኑ ዘውዴ የተደረገላቸውን ድጋፍ በማመስገን ድጋፉ ህብረተሰቡ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን መሆኑን በማሳየቱ መከላከያ ሰራዊቱ የገባውን ቃል በማክበር የሀገሩን የህግ የበላይነት ለማስከበርና የጀመረውን ተግባር በድል እንዲያጠናቅቅ የበለጠ ያነሳሳዋል ብለዋል ፡፡
በድጋፍ ስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተው የምርቃት ስነ ስርአት ያካሄዱት የአፍረን ቀሎ አባ ገዳ አቶ አብዱረዛቅ አህመድ እንደተናገሩት መከላከያ ሰራዊቱ በርቱ ከናንተ ወደኋላ የምንለው የለንም በማለት መንግስት በአሁኑ ሰአት እየወሰደ ላለው የህግን ማስከበር እርምጃ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በቀጣይም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡
የዋሄል ክላስተር አስተባባሪ እና የለገኦዳ ጉዱ ፈታህ ሊቀመንበር እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች ባስተላለፉት መልእክት የሀገር መከላከያ እያደረገ ላለው ተግባር ይሄ ያንስበታል እኛ ከህይወት መስዋዕትነት እስከ አለን ገንዘብ ድረስ ድጋፍ እናደርጋለን በማለት ይህ ጅማሮ በመሆኑ በቀጣይም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


